3. ለዐቅመ ቢሶችና ለድኻ አደጎች ፍረዱላቸው፤የችግረኛውንና የምስኪኑን መብት አስከብሩ።
4. ወገን የሌለውንና ችግረኛውን ታደጉ፤ከግፈኛውም እጅ አስጥሏቸው።
5. “ዕውቀትም ማስተዋልም የላቸውም፤በጨለማ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ይመላለሳሉ፤የምድርም መሠረቶች ሁሉ ተናወጡ።
6. “እኔም፤ ‘እናንተ አማልክት ናችሁ፤ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ’ አልሁ።
7. ነገር ግን እንደ ማንኛውም ሰው ትሞታላችሁ፤እንደ ማንኛውም ገዥ ትወድቃላችሁ።”
8. አምላክ ሆይ፤ ተነሥ፤ በምድር ላይ ፍረድ፤ሕዝቦች ሁሉ ርስትህ ናቸውና።