መዝሙር 81:6-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. “ትከሻውን ከሸክም ገላገልሁት፤እጁንም ቅርጫት ከመያዝ አሳረፍሁ።

7. በመከራህ ጊዜ ጠራኸኝ፤ እኔም ታደግሁህ፤በነጐድጓድ መሰወሪያ ውስጥ መለስሁልህ፤በመሪባ ውሃ ዘንድ ፈተንሁህ። ሴላ

8. “ሕዝቤ ሆይ፤ ሳስጠነቅቅህ ስማኝ፤እስራኤል ሆይ፤ ምነው ብታደምጠኝ!

9. በአንተ ዘንድ ባዕድ አምላክ አይኑር፤ለሌላም አምላክ አትስገድ።

10. ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ፣እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ፤አፍህን በሰፊው ክፈተው፤ እኔም እሞላዋለሁ።

መዝሙር 81