መዝሙር 81:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ብርታታችን ለሆነው አምላክ በደስታ ዘምሩ፤ለያዕቆብ አምላክ እልል በሉ።

2. ዝማሬውን ጀምሩ፤ ከበሮውን ምቱ፤በበገናና በመሰንቆ ጥዑም ዜማ አሰሙ።

3. በሙሉ ጨረቃ፣ በክብረ በዓላችን ዕለት፣በወሩ መግቢያ፣ ጨረቃ ስትወለድ መለከት ንፉ፤

4. ይህ ለእስራኤል የተሰጠ ሥርዐት፣የያዕቆብም አምላክ ድንጋጌ ነውና።

መዝሙር 81