መዝሙር 8:5-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ከመላእክት በጥቂት አሳነስኸው፤የክብርንና የሞገስን ዘውድ አቀዳጀኸው።

6. በእጆችህ ሥራ ላይ ሾምኸው፤ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛህለት፤

7. በጎችንና ላሞችን ሁሉ፣የዱር አራዊትንም፣

8. የሰማይ ወፎችንና፣የባሕር ዓሦችን፣በባሕር ውስጥ የሚርመሰመሱትንም ሁሉ አስገዛህለት።

9. እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ስምህ በምድር ሁሉ ላይ ምንኛ ግርማዊ ነው!

መዝሙር 8