መዝሙር 78:69-71 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

69. መቅደሱን እንደ ታላቅ ከፍታ፣ለዘላለም እንደ መሠረታት ምድር ሠራት።

70. ባሪያውን ዳዊትን መረጠ፤ከበጎች ጒረኖ ውስጥ ወሰደው፤

71. ለሕዝቡ ለያዕቆብ፣ለርስቱም ለእስራኤል እረኛ ይሆን ዘንድ፣የሚያጠቡ በጎችን ከመከተል አመጣው።

መዝሙር 78