መዝሙር 77:9-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. እግዚአብሔር ቸርነቱን ዘነጋ?ወይስ ከቍጣው የተነሣ ርኅራኄውን ነፈገ?።” ሴላ

10. እኔም፣ “የልዑል ቀኝ እጅ እንደ ተለወጠ ማሰቤ፣ይህ ድካሜ ነው” አልሁ።

11. የእግዚአብሔርን ሥራ አስታውሳለሁ፤የጥንት ታምራትህን በእርግጥ አስታውሳለሁ፤

12. ሥራህን ሁሉ አሰላስላለሁ፤ድንቅ ሥራህን ሁሉ አውጠነጥናለሁ።

መዝሙር 77