መዝሙር 77:2-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. በመከራዬ ቀን እግዚአብሔርን ፈለግሁት፤በሌሊትም ያለ ድካም እጆቼን ዘረጋሁ፤ነፍሴም አልጽናና አለች።

3. አምላክ ሆይ፤ አንተን ባሰብሁ ቍጥር ቃተትሁ፤ባወጣሁ ባወረድሁም መጠን መንፈሴ ዛለች። ሴላ

4. ዐይኖቼ እንዳይከደኑ ያዝሃቸው፤መናገር እስኪሳነኝ ድረስ ታወክሁ።

መዝሙር 77