መዝሙር 76:4-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. አንተ ብርሃን ተላብሰህ ደምቀሃል፤ግርማዊነትህም ከዘላለም ተራሮች ይልቃል።

5. ልበ ሙሉ የሆኑት ተዘርፈዋል፤አንቀላፍተውም ተኝተዋል፤ከጦረኞቹም መካከል፣እጁን ማንቀሳቀስ የቻለ የለም።

6. የያዕቆብ አምላክ ሆይ፤ ከተግሣጽህ የተነሣ፣ፈረስና ፈረሰኛው ጭልጥ ብለው ተኝተዋል።

7. መፈራት ያለብህ አንተ ብቻ ነህ፤በተቈጣህ ጊዜ ማን በፊትህ መቆም ይችላል?

8. አንተ ፍርድን ከሰማይ አሰማህ፤ምድርም ፈርታ ጸጥ አለች፤

9. አምላክ ሆይ፤ ይህም የሆነው አንተ የምድር ጐስቋሎችን ለማዳን፣ለፍርድ በተነሣህ ጊዜ ነው። ሴላ

10. ሰውን ብትቈጣ እንኳ ለክብርህ ይሆናል፤ከቍጣ የተረፉትንም ትገታቸዋለህ።

መዝሙር 76