መዝሙር 75:8-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. በእግዚአብሔር እጅ ጽዋ አለ፤በሚገባ የተቀመመና ዐረፋ የሚወጣው የወይን ጠጅ ሞልቶበታል፤ይህን ከውስጡ ወደ ውጭ ገለበጠው፤የምድር ዐመፀኞችም አተላው ሳይቀር ይጨልጡታል።

9. እኔ ግን ይህን ለዘላለም ዐውጃለሁ፤ለያዕቆብም አምላክ ዝማሬ አቀርባለሁ።

10. የክፉዎችን ሁሉ ቀንድ እሰብራለሁ፤የጻድቃን ቀንድ ግን ከፍ ከፍ ይላል።

መዝሙር 75