መዝሙር 75:3-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ምድርና ሕዝቦቿ ሁሉ በሚናወጡበት ጊዜ፣ምሰሶቿን አጽንቼ የምይዝ እኔ ነኝ። ሴላ

4. እብሪተኛውን፣ ‘አትደንፋ’፤ክፉውንም ‘ቀንድህን ከፍ አታድርግ እለዋለሁ፤

5. ቀንድህን ወደ ሰማይ አታንሣ፤ዐንገትህንም መዝዘህ አትናገር።’ ”

6. ክብር ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ፣ወይም ከምድረ በዳ አይመጣምና፤

7. ነገር ግን የሚፈርድ እግዚአብሔር ነው፤እርሱ አንዱን ዝቅ፣ ሌላውን ከፍ ያደርጋል።

መዝሙር 75