መዝሙር 74:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አምላክ ሆይ፤ ለዘላለም የጣልኸን ለምንድን ነው?በማሰማሪያህ ባሉ በጎችህስ ላይ ቍጣህ ለምን ነደደ?

2. ጥንት ገንዘብህ ያደረግሃትን ጉባኤ፣የዋጀሃትን የርስትህን ነገድ፣መኖሪያህ ያደረግሃትን የጽዮን ተራራ አስብ።

3. እርምጃህን ለዘላለሙ ባድማ ወደ ሆነው አቅና፤ጠላት በመቅደስህ ውስጥ ያለውን ሁሉ አበላሽቶአል።

መዝሙር 74