መዝሙር 73:18-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. በእርግጥ በሚያዳልጥ ስፍራ አስቀመጥኻቸው፤ወደ ጥፋትም አወረድሃቸው።

19. እንዴት ፈጥነው በቅጽበት ጠፉ!በድንጋጤ ፈጽመው ወደሙ።

20. ሰው ከሕልሙ ሲነቃ እንደሚሆነው፣ጌታ ሆይ፤ አንተም በምትነሣበት ጊዜ፣እንደ ቅዠት ከንቱ ታደርጋቸዋለህ።

21. ነፍሴ በተማረረች ጊዜ፣ልቤም በተቀሠፈ ጊዜ፣

22. ስሜት የሌለውና አላዋቂ ሆንሁ፤በፊትህም እንደ እንስሳ ሆንሁ።

መዝሙር 73