መዝሙር 73:12-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. እንግዲህ፣ ክፉዎች ይህን ይመስላሉ፤ሁል ጊዜ ግድ የለሽና ሀብት በሀብት ናቸው።

13. ለካ ልቤን ንጹሕ ያደረግሁት በከንቱ ነው፤እጄንም በየዋህነት የታጠብሁት በከንቱ ኖሮአል!

14. ቀኑን ሙሉ ተቀሠፍሁ፤ጠዋት ጠዋትም ተቀጣሁ።

15. “እኔ እንደዚህ እናገራለሁ” ብልማ ኖሮ፣የልጆችህን ትውልድ በከዳሁ ነበር።

16. ይህን ነገር ለመረዳት በሞከርሁ ጊዜ፣አድካሚ ተግባር መስሎ ታየኝ።

መዝሙር 73