1. እግዚአብሔር ልባቸው ንጹሕ ለሆነ፣ለእስራኤል እንዴት ቸር ነው!
2. እኔ ግን እግሬ ሊሰናከል፣አዳልጦኝም ልወድቅ ጥቂት ቀረኝ።
3. ክፉዎች ሲሳካላቸው አይቼ፣በዐመፀኞች ቀንቼ ነበርና።
4. አንዳች ጣር የለባቸውም፤ሰውነታቸውም ጤናማና የተደላደለ ነው።
5. በሰዎች የሚደርሰው ጣጣ አይደርስባቸውም፤እንደ ማንኛውም ሰው መከራ አያገኛቸውም።
6. ስለዚህ ትዕቢት የዐንገት ጌጣቸው ነው፤ዐመፅንም እንደ ልብስ ተጐናጽፈዋል።