3. ተራሮች ብልጽግናን፣ኰረብቶችም የጽድቅን ፍሬ ለሕዝቡ ያመጣሉ።
4. ለተቸገረው ሕዝብ ይሟገታል፤የድኾችን ልጆች ያድናል፤ጨቋኙንም ያደቀዋል።
5. ፀሓይ እስካለች ድረስ፣ጨረቃም በምትኖርበት ዘመን ሁሉ፣ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።
6. እንደ ዝናብ በታጨደ መስክ ላይ ይወርዳል፤እንደ ካፊያም ምድርን ያረሰርሳል።
7. በዘመኑ ጽድቅ ይሰፍናል፤ጨረቃ ከስፍራዋ እስከምትታጣ ድረስም ሰላም ይበዛል።
8. ከባሕር እስከ ባሕር ድረስ፣ከታላቁም ወንዝ እስከ ምድር ዳርቻ ይገዛል።