መዝሙር 71:22-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. አምላኬ ሆይ፤ ስለ ታማኝነትህ፣በበገና አመሰግንሃለሁ፤የእስራኤል ቅዱስ ሆይ፤በመሰንቆ እዘምርልሃለሁ።

23. ዝማሬ በማቀርብልህ ጊዜ ከንፈሮቼ በደስታ ይሞላሉ፤አንተ የተቤዠሃትም ነፍሴ እልል ትላለች።

24. አንደበቴ ስለ ጽድቅህ፣ቀኑን ሙሉ ያወራል፤የእኔን መጐዳት የሚፈልጉ፣አፍረዋልና፤ ተዋርደዋልም።

መዝሙር 71