መዝሙር 69:21-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. ምግቤን ከሐሞት ቀላቀሉ፤ለጥማቴም ሆምጣጤ ሰጡኝ።

22. የቀረበላቸው ማእድ ወጥመድ ይሁንባቸው፤ለማኅበራቸውም አሽክላ ይሁን።

23. ዐይኖቻቸው እንዳያዩ ይጨልሙ፤ጀርባቸውም ዘወትር ይጒበጥ።

24. መዓትህን በላያቸው አፍስስ፤የቍጣህም መቅሠፍት ድንገት ይድረስባቸው።

25. ሰፈራቸው ባድማ ይሁን፤በድንኳኖቻቸው የሚኖር አይገኝ፤

26. አንተ የመታኻቸውን አሳደዋልና፤ያቈሰልኻቸውንም ሥቃያቸውን አባብሰዋል።

27. በበደላቸው በደል ጨምርባቸው፤ወደ ጽድቅህም አይግቡ።

28. ከሕይወት መጽሐፍ ይደምሰሱ፤ከጻድቃንም ጋር አይጻፉ።

29. ነገር ግን እኔ በሥቃይና በጭንቅ ላይ እገኛለሁ፤አምላክ ሆይ፤ ማዳንህ ደግፎ ይያዘኝ።

መዝሙር 69