መዝሙር 69:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አምላክ ሆይ፤ አድነኝ፤ውሃ እስከ ዐንገቴ ደርሶብኛልና።

2. የእግር መቆሚያ በሌለው፣በጥልቅ ረግረግ ውስጥ ሰጥሜአለሁ፤ወደ ጥልቅ ውሃ ገባሁ፤ሞገዱም አሰጠመኝ።

3. በጩኸት ደከምሁ፤ጉሮሮዬም ደረቀ፤አምላኬን በመጠባበቅ፣ዐይኖቼ ፈዘዙ።

4. ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ፣ከራሴ ጠጒር በዙ፤ሕይወቴን ለማጥፋት የሚፈልጉ፣በከንቱም የሚጠሉኝ ብዙዎች ሆኑ፤ያልሰረቅሁትን ነገር፣መልሰህ አምጣ ተባልሁ።

5. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ሞኝነቴን ታውቃለህ፤በደሌም ከአንተ የተሰወረ አይደለም።

6. ጌታ የሰራዊት አምላክ ሆይ፤አንተን ተስፋ የሚያደርጉ፣በእኔ ምክንያት አይፈሩ፤የእስራኤል አምላክ ሆይ፤አንተን አጥብቀው የሚሹ፣ከእኔ የተነሣ አይዋረዱ።

መዝሙር 69