መዝሙር 67:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ይማረን፤ ይባርከን፤ፊቱንም በላያችን ያብራ፤ ሴላ

2. መንገድህ በምድር ላይ፣ማዳንህም በሕዝቦች ሁሉ መካከል ይታወቅ ዘንድ።

3. እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰዎች ያመስግኑህ፤ሰዎች ሁሉ ምስጋና ያቅርቡልህ።

መዝሙር 67