መዝሙር 65:4-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. አንተ የመረጥኸው፣ ወደ ራስህ ያቀረብኸው፣በአደባባይህም ያኖርኸው ምስጉን ነው!ከተቀደሰው መቅደስህ፣ከቤትህም በረከት እንረካለን።

5. እግዚአብሔር አዳኛችን ሆይ፤በጽድቅ ድንቅ አሠራር መልስልን፤አንተ ለምድር ዳርቻ ሁሉ፣በርቀት ላለውም ባሕር ተስፋ ነህ።

6. ተራሮችን በብርታትህ መሠረትህ፤ኀይልንም ታጥቀሃል።

7. አንተ የባሕሮችን ማስገምገም፣የማዕበላቸውን ፉጨት፣የሕዝቦችንም ሁከት ጸጥ ታደርጋለህ።

8. ርቀው በምድር ዳርቻ ያሉት ከድንቅ ሥራህ የተነሣ ይደነግጣሉ፤የንጋትንና የምሽትን መምጫዎች፣በደስታ እልል እንዲሉ ታደርጋቸዋለህ።

9. ምድርን ትጐበኛለህ፤ ታጠጣለህም፤እጅግ ታበለጽጋታለህም።ለሰዎች እህልን ይለግሱ ዘንድ፣የእግዚአብሔር ወንዞች ውሃን የተሞሉ ናቸው፤አንተ እንዲህ እንዲሆን ወስነሃልና።

10. ትልሟን በውሃ ታረሰርሳለህ፤ቦይዋን ታስተካክላለህ፤በካፊያ ታለሰልሳለህ፤ቡቃያዋንም ትባርካለህ።

11. ለዘመኑ በጎነትህን ታጐናጽፈዋለህ፤ሠረገላህም በረከትን ተሞልቶ ይፈስሳል።

12. የምድረ በዳው ሣር እጅግ ለመለመ፤ኰረብቶችም ደስታን ተጐናጸፉ።

መዝሙር 65