መዝሙር 63:6-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. በመኝታዬ አስብሃለሁ፤ሌሊቱንም ሁሉ ስለ አንተ አሰላስላለሁ።

7. አንተ ረዳቴ ነህና፣በክንፎችህ ሥር ተጠልዬ በደስታ እዘምራለሁ።

8. ነፍሴ አንተን የሙጥኝ ብላለች፤ቀኝ እጅህም ደግፋ ይዛኛለች።

9. ነፍሴን ለማጥፋት የሚሹ ግን፣ወደ ምድር ጥልቅ ይወርዳሉ፤

10. ለሰይፍ አልፈው ይሰጣሉ፤የቀበሮዎችም ምግብ ይሆናሉ።

11. ንጉሥ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል፤በእግዚአብሔርም ስም ቃል የሚገቡ ሁሉ ይከብራሉ፤የሐሰተኞች አንደበትም ትዘጋለች።

መዝሙር 63