መዝሙር 62:10-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. በዝርፊያ አትታመኑ፤በቅሚያም ተስፋ አታድርጉ፤በዚህ ብትበለጽጉም፣ልባችሁ ይህን አለኝታ አያድርግ።

11. እግዚአብሔር አንድ ነገር ተናገረ፤እኔም ይህን ሁለት ጊዜ ሰማሁ፤ኀይል የእግዚአብሔር ነው።

12. ጌታ ሆይ፤ ምሕረትም የአንተ ነው፤አንተ ለእያንዳንዱ፣እንደ ሥራው ትከፍለዋለህ።

መዝሙር 62