መዝሙር 60:2-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. ምድሪቱን አናወጥሃት፤ ፍርክስክስ አደረግሃት፤ትንገዳገዳለችና ስብራቷን ጠግን።

3. ለሕዝብህ አበሳውን አሳየኸው፤ናላ የሚያዞር የወይን ጠጅ እንድንጠጣም ሰጠኸን።

4. ነገር ግን ከቀስት እንዲያመልጡ፣ለሚፈሩህ ምልክት አቆምህላቸው። ሴላ

5. ወዳጆችህ ይድኑ ዘንድ፣በቀኝ እጅህ ርዳን፤ መልስም ስጠን።

6. እግዚአብሔር ከመቅደሱ እንዲህ ሲል ተናገረ፤“ደስ እያለኝ የሴኬምን ምድር እሸነሽናለሁ፤የሱኮትን ሸለቆ አከፋፍላለሁ።

መዝሙር 60