መዝሙር 59:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አምላክ ሆይ፤ ከጠላቶቼ እጅ አድነኝ፤ሊያጠቁኝ ከሚነሡብኝም ጠብቀኝ።

2. ከክፉ አድራጊዎች ታደገኝ፤ደም ከተጠሙ ሰዎችም አድነኝ።

3. እነሆ በነፍሴ ላይ አድብተዋልና፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጨካኞች ያለ በደሌ፣ ያለ ኀጢአቴበላዬ ተሰብስበው ዶለቱብኝ።

4. እነርሱ ያለ በደሌ ሊያጠቁኝ ተዘጋጅተው መጡ፤አንተ ግን ትረዳኝ ዘንድ ተነሥ፤ ሁኔታዬንም ተመልከት።

5. የሰራዊት አምላክ የሆንህ፣ አንተ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ሕዝቦችን ሁሉ ለመቅጣት ተነሥ፤በተንኰላቸው በደል የሚፈጽሙትንም ሁሉ አትማራቸው። ሴላ

መዝሙር 59