መዝሙር 58:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ኀያላን ሆይ፤ በውኑ ጽድቅ ከአፋችሁ ይወጣል?የሰው ልጆች ሆይ፤ በቅን ትፈርዳላችሁን?

2. የለም፤ በልባችሁ ክፋትን ታውጠነጥናላችሁ፤በእጃችሁም ዐመፅን በምድር ላይ ትጐነጒናላችሁ።

3. ክፉዎች በማሕፀን ሳሉ ከመንገድ የወጡ ናቸው፤ሲወለዱ ጀምሮ የተሳሳቱና ውሸታሞች ናቸው።

መዝሙር 58