መዝሙር 56:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ የሰዎች መረገጫ ሆኛለሁና ማረኝ፤ቀኑንም ሙሉ በውጊያ አስጨንቀውኛል።

2. ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ በላዬ ቆሙ፤በትዕቢት የሚዋጉኝ ብዙዎች ናቸውና።

3. ፍርሀት በሚይዘኝ ጊዜ፣እምነቴን በአንተ ላይ አደርጋለሁ።

መዝሙር 56