መዝሙር 55:15-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ሞት ሳይታሰብ ድንገት ይምጣባቸው፤በሕይወት ሳሉ ወደ ሲኦል ይውረዱ፤ክፋት በመካከላቸው አድራለችና።

16. እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር እጣራለሁ፤ እግዚአብሔርም ያድነኛል።

17. በማታ፣ በጥዋትና በቀትር፣እጮኻለሁ፤ እቃትታለሁም፤እርሱም ድምፄን ይሰማል።

18. በተቃውሞ የተነሡብኝ ብዙዎች ናቸውና፣ከተቃጣብኝ ጦርነት፣ነፍሴን በሰላም ይቤዣታል።

19. አካሄዳቸውን አልቀየሩምና፣እግዚአብሔርንም አልፈሩትምና፣ከጥንት ጀምሮ በዙፋኑ ላይ ያለ አምላክ፣ ሴላሰምቶ ያዋርዳቸዋል።

20. ባልንጀራዬ የምለው ሰው እጁንበወዳጆቹ ላይ ሰነዘረ፤ቃል ኪዳኑንም አፈረሰ።

መዝሙር 55