መዝሙር 55:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ልመናዬን ቸል አትበል፤

2. ወደ እኔ ተመልከት፤ መልስልኝም።በውስጤ ታውኬአለሁ፤ ተናውጬአለሁም፤

3. በጠላት ድምፅ ተሸበርሁ፤በክፉዎች ድንፋታ ደነገጥሁ፤መከራ አምጥተውብኛልና፤በቍጣም ተነሣሥተው ጠላት ሆነውብኛል።

4. ልቤ በውስጤ ተጨነቀብኝ፤የሞት ድንጋጤም በላዬ መጣ።

መዝሙር 55