መዝሙር 48:5-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. አይተውም ተደነቁ፤ደንግጠውም ፈረጠጡ።

6. ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣በዚያ ብርክ ያዛቸው።

7. የምሥራቅ ነፋስ የተርሴስን መርከብ እንደሚሰባብር፣አንተ አብረከረክሃቸው።

8. እንደ ሰማን፣በሰራዊት አምላክ ከተማ፣በአምላካችን ከተማ፣እንዲሁ አየን፤እግዚአብሔር ለዘላለም ያጸናታል። ሴላ

9. አምላክ ሆይ፤ በቤተ መቅደስህ ውስጥ ሆነን፣ምሕረትህን እናስባለን።

መዝሙር 48