መዝሙር 48:11-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ስለ ፍርድህ፣የጽዮን ተራራ ሐሤት ታድርግ፤የይሁዳ መንደሮችም ደስ ይበላቸው።

12. በጽዮን አካባቢ ተመላለሱ፤ ዙሪያዋንም ሂዱ፤የጥበቃ ግንበኞቿንም ቍጠሩ፤

13. ለሚቀጥለው ትውልድ ትናገሩ ዘንድ፣መከላከያ ዕርዶቿን ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፤መጠበቂያ ማማዎቿን እዩ።

14. ይህ አምላክ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላካችን ነውና፤እስከ መጨረሻው የሚመራንም እርሱ ነው።

መዝሙር 48