መዝሙር 45:3-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ኀያል ሆይ፤ ሰይፍህን በወገብህ ታጠቅ፤ግርማ ሞገስንም ተላበስ።

4. ስለ እውነት፣ ስለ ትሕትና ስለ ጽድቅ፣ሞገስን ተጐናጽፈህ በድል አድራጊነት ገሥግሥ፤ቀኝ እጅህም ድንቅ ተግባር ታሳይ።

5. የሾሉ ፍላጻዎችህ በንጉሥ ጠላቶች ልብ ይሰካሉ፤ሕዝቦችም ከእግርህ በታች ይወድቃሉ።

6. አምላክ ሆይ፤ ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይኖራል፤የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ናት።

መዝሙር 45