መዝሙር 44:12-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. ሕዝብህን በርካሽ ዋጋ ሸጥኸው፤ከሽያጩም ያገኘኸው ትርፍ የለም።

13. ለጎረቤቶቻችን ስድብ፣በዙሪያችን ላሉትም መሣቂያና መዘበቻ አደረግኸን።

14. በሕዝቦች ዘንድ መተረቻ፣በሰዎች መካከል በንቀት ራስ መነቅነቂያ አደረግኸን።

15. ውርደቴ ቀኑን ሙሉ በፊቴ ነው፤ፊቴም ዕፍረትን ተከናንቦአል።

መዝሙር 44