መዝሙር 40:10-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ጽድቅህን በልቤ አልሸሸግሁም፤ታማኝነትህንና ማዳንህን እናገራለሁ፤ምሕረትህንና እውነትህን፣ከታላቅ ጉባኤ አልደበቅሁም።

11. እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህን አትንፈገኝ፤ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ይጠብቁኝ፤

12. ስፍር ቍጥር የሌለው ክፋት ከቦኛልና፤የኀጢአቴ ብዛት ስለ ያዘኝ ማየት ተስኖኛል፤ከራሴ ጠጒር ይልቅ በዝቶአል፤ልቤም ከድቶኛል።

13. እግዚአብሔር ሆይ፤ ታድነኝ ዘንድ ፈቃድህ ይሁን፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።

መዝሙር 40