መዝሙር 38:4-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. በደሌ ውጦኛል፤እንደ ከባድ ሸክምም ተጭኖኛል።

5. ከንዝህላልነቴ የተነሣ፣ቍስሌ ሸተተ፤ መገለም፤

6. ዐንገቴን ደፋሁ፤ ጐበጥሁም፤ቀኑንም ሙሉ በትካዜ ተመላለስሁ።

7. ወገቤ እንደ እሳት ነዶአል፤ሰውነቴም ጤና የለውም።

8. እጅግ ዝያለሁ፤ ፈጽሞም ደቅቄአለሁ፤ከልቤም መታወክ የተነሣ እጮኻለሁ።

9. ጌታ ሆይ፤ ምኞቴ ሁሉ በፊትህ ግልጽ ነው፤ጭንቀቴም ከአንተ የተሰወረ አይደለም።

10. ልቤ በኀይል ይመታል፤ ጒልበት ከድቶኛል፤የዐይኔም ብርሃን ጠፍቶአል።

11. ከቊስሌ የተነሣ ወዳጆቼም ባልንጀሮቼም ሸሹኝ፤ጎረቤቶቼም ርቀው ቆሙ።

መዝሙር 38