መዝሙር 38:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ በቍጣህ አትገሥጸኝ፤በመዓትህም አትቅጣኝ።

2. ፍላጻዎችህ ወግተውኛልና፤እጅህም ተጭናኛለች።

3. ከቍጣህ የተነሣ ሰውነቴ ጤና አጥቶአል፤ከኀጢአቴም የተነሣ ዐጥንቶቼ ሰላም የላቸውም።

4. በደሌ ውጦኛል፤እንደ ከባድ ሸክምም ተጭኖኛል።

5. ከንዝህላልነቴ የተነሣ፣ቍስሌ ሸተተ፤ መገለም፤

6. ዐንገቴን ደፋሁ፤ ጐበጥሁም፤ቀኑንም ሙሉ በትካዜ ተመላለስሁ።

መዝሙር 38