መዝሙር 37:31-33 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

31. የአምላኩ ሕግ በልቡ አለ፤አካሄዱም አይወላገድም።

32. ክፉዎች ጻድቁን ይከታተሉታል፤ሊገድሉትም ይሻሉ።

33. እግዚአብሔር ግን በእጃቸው አይጥለውም፤ፍርድ ፊት ሲቀርብም አሳልፎ አይሰጠውም።

መዝሙር 37