መዝሙር 37:29-32 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

29. ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፤በእርሷም ለዘላለም ይኖራሉ።

30. የጻድቅ አፍ ጥበብን ይናገራል፤አንደበቱም ፍትሐዊ ነገር ያወራል።

31. የአምላኩ ሕግ በልቡ አለ፤አካሄዱም አይወላገድም።

32. ክፉዎች ጻድቁን ይከታተሉታል፤ሊገድሉትም ይሻሉ።

መዝሙር 37