1. ክፉውን ሰው፣በደል በልቡ ታናግረዋለች፤እግዚአብሔርን መፍራት፣በፊቱ የለም፤
2. በደሉ ግልጽ ወጥቶ እንዳይጠላ፣ራሱን በራሱ እጅግ ይሸነግላልና።
3. ከአንደበቱ የሚወጣው የክፋትና የተንኰል ቃል ነው፤ማስተዋልንና በጎ ማድረግን ትቶአል።
4. በመኝታው ላይ ክፋትን ያውጠነጥናል፤ራሱን በጎ ባልሆነ መንገድ ይመራል፤ክፋትንም አያርቅም።
5. እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ እስከ ሰማያት ይደርሳል፤ታማኝነትህም እስከ ጠፈር ይመጥቃል።
6. ጽድቅህ እንደ ታላላቅ ተራሮች፣ፍርድህም እጅግ ጥልቅ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ሰውንም እንስሳንም ታድናለህ።
7. አምላክ ሆይ፤ ምሕረትህ እንዴት ክቡር ነው!የሰዎች ልጆች ሁሉ፣በክንፎችህ ጥላ ሥር መጠጊያ ያገኛሉ።