መዝሙር 35:21-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. አፋቸውን አስፍተው ከፈቱብኝ፤“ዕሠይ! ዕሠይ! በዐይናችን አየነው” አሉ።

22. እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን አይተሃልና ዝም አትበል፤ጌታ ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ።

23. አምላኬ፣ ጌታዬ፤ ለእኔ ለመሟገት ተነሥ!ልትከራከርልኝም ተንቀሳቀስ።

24. እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ በጽድቅህ ፍረድልኝ፤በእኔም ላይ ደስ አይበላቸው።

መዝሙር 35