መዝሙር 35:2-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. ትልቁንና ትንሹን ጋሻ ያዝ፤እኔንም ለመርዳት ተነሥ።

3. በሚያሳድዱኝ ላይ፣ጦርና ጭሬ ምዘዝ፤ነፍሴንም፣“የማድንሽ እኔ ነኝ” በላት።

4. ሕይወቴን የሚፈልጓት፣ይቅለሉ፣ ይዋረዱ፤እኔን ለማጥፋት የሚያሤሩ፣ዐፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።

5. በነፋስ ፊት እንዳለ እብቅ ይሁኑ፤ የእግዚአብሔር መልአክ ያሳዳቸው።

መዝሙር 35