መዝሙር 35:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ የሚታገሉኝን ታገላቸው፤የሚዋጉኝንም ተዋጋቸው።

2. ትልቁንና ትንሹን ጋሻ ያዝ፤እኔንም ለመርዳት ተነሥ።

3. በሚያሳድዱኝ ላይ፣ጦርና ጭሬ ምዘዝ፤ነፍሴንም፣“የማድንሽ እኔ ነኝ” በላት።

4. ሕይወቴን የሚፈልጓት፣ይቅለሉ፣ ይዋረዱ፤እኔን ለማጥፋት የሚያሤሩ፣ዐፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።

መዝሙር 35