መዝሙር 33:16-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. ንጉሥ በሰራዊቱ ታላቅነት አይድንም፤ጀግናም በኀይሉ ብርታት አያመልጥም።

17. በፈረስ ድል አደርጋለሁ ማለት ከንቱ ተስፋ ነው፤በብርቱ ጒልበቱም ማንንም አያድንም።

18. እነሆ፤ የእግዚአብሔር ዐይኖች በሚፈሩት ላይ ናቸው፤ምሕረቱንም በሚጠባበቁት ላይ አትኵረዋል።

19. በዚህም ነፍሳቸውን ከሞት ያድናል፤በራብ ዘመንም በሕይወት ያኖራቸዋል።

መዝሙር 33