መዝሙር 32:3-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ቀኑን ሙሉ ከመቃተቴ የተነሣ፣ዝም ባልሁ ጊዜ፣ዐጥንቶቼ ተበላሹ፤

4. በቀንና በሌሊት፣እጅህ ከብዳብኛለችና፤ኀይሌም የበጋ ትኵሳት እንደላሰው ነገር፣ከውስጤ ተሟጠጠ። ሴላ

5. ኀጢአቴን ለአንተ አስታወቅሁ፤በደሌንም አልሸሸግሁም፤ደግሞም “መተላለፌን ለእግዚአብሔር እናዘዛለሁ” አልሁ፤አንተም የኀጢአቴን በደል፣ይቅር አልህ። ሴላ

6. ስለዚህ ጻድቅ ሁሉ፣በጭንቅ ጊዜ ወደ አንተ ይጸልይ፤ኀይለኛ ጐርፍ አካባቢውን ቢያጥለቀልቅም፣እርሱ አጠገብ አይደርስም።

መዝሙር 32