መዝሙር 31:17-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. እግዚአብሔር ሆይ፤ወደ አንተ እጮኻለሁና አልፈር፤ክፉዎች ግን ይፈሩ፤ሲኦል ገብተውም ጸጥ ይበሉ።

18. በጻድቁ ላይ በእብሪት የሚናገሩ፣ትዕቢትንና ንቀትን የተሞሉ፣ዋሾ ከንፈሮች ድዳ ይሁኑ።

19. በሰዎች ልጆች ፊት፣ለሚፈሩህ ያስቀመጥሃት፣መጠጊያ ላደረጉህም ያዘጋጀሃት፣በጎነትህ ምንኛ በዛች!

መዝሙር 31