መዝሙር 31:14-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ፤“አንተ አምላኬ ነህ” እልሃለሁም።

15. ዘመኔ ያለው በእጅህ ነው፤ከጠላቶቼ እጅ ታደገኝ፤ከሚያሳድዱኝም አድነኝ።

16. ፊትህን በአገልጋይህ ላይ አብራ፤በምሕረትህም አድነኝ።

17. እግዚአብሔር ሆይ፤ወደ አንተ እጮኻለሁና አልፈር፤ክፉዎች ግን ይፈሩ፤ሲኦል ገብተውም ጸጥ ይበሉ።

18. በጻድቁ ላይ በእብሪት የሚናገሩ፣ትዕቢትንና ንቀትን የተሞሉ፣ዋሾ ከንፈሮች ድዳ ይሁኑ።

መዝሙር 31