መዝሙር 30:8-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ ተጣራሁ፤ወደ ጌታም እንዲህ ብዬ ጮኽሁ፤

9. “በእኔ ወደ ጒድጓድ መውረድ፣በመሞቴ ምን ጥቅም ይገኛል?ዐፈር ያመሰግንሃልን?ታማኝነትህንስ ይናገራልን?

10. እግዚአብሔር ሆይ፤ ስማ፤ ማረኝም፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ረዳት ሁነኝ።”

11. ዋይታዬን ወደ ሽብሸባ ለወጥህልኝ፤ማቄን አውልቀህ ፍስሓን አለበስኸኝ፤

12. እንግዲህ ነፍሴ ታመስግንህ፤ ዝምም አትበል፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ለዘላለም አመሰግንሃለሁ።

መዝሙር 30