መዝሙር 30:3-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. እግዚአብሔር ሆይ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት፤ወደ ጒድጓድ ከመውረድም መልሰህ ሕያው አደረግኸኝ።

4. እናንተ ቅዱሳኑ፤ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ቅዱስ ስሙንም አወድሱ።

5. ቊጣው ለዐጭር ጊዜ ነው፤ቸርነቱ ግን እስከ ዕድሜ ልክ ነውና፤ሌሊቱን በልቅሶ ቢታደርም፣በማለዳ ደስታ ይመጣል።

6. እኔም በተረጋጋሁ ጊዜ፣“ከቶ አልናወጥም” አልሁ።

7. እግዚአብሔር ሆይ፤ በአንተ ሞገስ፣ተራሮቼ ጸኑ፣ፊትህን በሰወርህ ጊዜ ግን፣ውስጤ ታወከ።

መዝሙር 30