መዝሙር 29:9-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. የእግዚአብሔር ድምፅ ወርካዎችን ይወዘውዛል፤ጫካዎችንም ይመነጥራል፤ሁሉም በእርሱ ቤተ መቅደስ ሆኖ “ይክበር!” ይላል።

10. እግዚአብሔር በጐርፍ ላይ ዙፋኑን ዘርግቶ ተቀምጦአል፤ እግዚአብሔር በንጉሥነቱ ለዘላለም በዙፋኑ ላይ ይቀመጣል።

11. እግዚአብሔር ለሕዝቡ ብርታትን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን በሰላም ይባርካል።

መዝሙር 29