መዝሙር 29:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እናንተ ኀያላን፣ ለእግዚአብሔር ስጡ፤ክብርንና ብርታትን ለእግዚአብሔር ስጡ።

2. ለስሙ የሚገባ ክብር ለእግዚአብሔር ስጡ፤በቅድስናው ግርማ ለእግዚአብሔር ስገዱ።

3. የእግዚአብሔር ድምፅ በውሆች ላይ ነው፤የክብር አምላክ አንጐደጐደ፤ እግዚአብሔር በታላላቅ ውሆች ላይ አንጐደጐደ።

መዝሙር 29