መዝሙር 28:6-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. የልመናዬን ቃል ሰምቶአልና፣ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን።

7. እግዚአብሔር ብርታቴና ጋሻዬ ነው፤ልቤ በእርሱ ይታመናል፤ እርሱም ዐግዞኛል፤ልቤ ሐሤት አደረገ፤በዝማሬም አመሰግነዋለሁ።

8. እግዚአብሔር ለሕዝቡ ብርታታቸው ነው፤ለቀባውም የመዳን ዐምባ ነው።

9. ሕዝብህን አድን፤ ርስትህንም ባርክ፤እረኛ ሁናቸው፤ ለዘላለሙም ዐቅፈህ ያዛቸው።

መዝሙር 28